አብርሆት ቤተ- መፃሕፍት ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ በዓለማቀፍ ደረጃ መጽሐፍትን ለማሰብሰብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከተለያዩ አምባሳደሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። አስራ አንድ የሚሆኑ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች አብርሆትን የጐበኙ ሲሆን በተለያዩ ቋንቋዎች የተፃፉ በርካታ መጽሐፍትንም በ ስጦታ አበርክተዋል።
በኢትዮጵያ የሜክሲኮ እንዲሁም በ ኢትዮጵያ የኡራጉአይ አምባሳደሮች ቤተመጽሐፍቱ ያለበትን ደረጀ አድንቀዋል።
በተጨማሪም አምባሳደሮቹ ከ ኢንጀነር ውብአየሁ ጋር ለወደፊት የበለጠ ግንኙነት መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ መክረዋል።
Director of Abrehot Library, Engineer Wubayehu Mamo, discussed with various ambassadors on the possibility of collecting books on international level. Eleven ambassadors from different countries to Ethiopia visited Abrehot and donated considerable number of books written in different languages . The ambassadors of Mexico and Uraguay to Ethiopia appreciated the current state of the library. In addition, the ambassadors advised on the possibility of establishing more relations with Engineer Wubayehu in the future.
ብርሀን ለኢትዮጵያ 🇪🇹
Enlightenment for Ethiopia 🇪🇹