Skip to content Skip to sidebar Skip to footer

የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ውባአየሁ ማሞ በበኩላቸው ብሬል ዓይነ ስውራን ህልማቸውንና ምኞታቸውን እንዲያሳኩ በማበረታታት በርካታ ዕድሎችን መክፈቱን አመልክተዋል።

ብሬል በሥነ-ጽሑፍ ዘርፍ በዓለም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ችሏልም ነው ያሉት።

የብሬል ቀን የማብቃት፣ የመደመርና የተደራሽነት በዓል መሆኑን ገልጸው በኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን እኩል የትምህርት፣ የሥራና የባህል ልምምድ እንዲያገኙ መደገፍ የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ረታ እንደገለጹት ብሬል የዓይነ ስውራንን የመማር፣ የመናገርና ኃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶችን ያረጋገጠ ነው።

በኢትዮጵያ የብሬል ትምህርት መሻሻሎች መኖራቸውን ገልጸው የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን በልዩ የትምህርት ፍላጎት በየአካባቢያቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እየተማሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በማኅበሩ የብሬል ሕትመት አስተባባሪ ምሥራቅ አራጌ የብሬል ሕትመት መሻሻል በመሳየቱ አንድ መጻሕፍ ለማሳተም ስድስት ወር ይፈጅ የነበረው አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ መታተም መቻሉን ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በብሬል ሊዘጋጁ ያልቻሉ ጽሑፎች በብሬል ተዘጋጅተው ተደራሽ መሆን መቻላቸውንም ጠቁመዋል።

የዓለም የብሬል ቀን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጃኑዋሪ 4 በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን ብሬልን የፈጠረውን ልዊስ ብሬልን ለማስታወስና ዓይነ ስውራን ለማንበብና ለመጻፍ የሚጠቀሙበትን ብሬልን ውለታ የሚወሳበት ነው።

Amharic English