Skip to content Skip to sidebar Skip to footer

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ከአምስት ሺህ በላይ መጽሀፍት አስረከበ

ሚያዚያ 18/2014/ኢዜአ/ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ያሰባሰበውን ከአምስት ሺህ በላይ መጽሀፍት አስረከበ፡፡

መጽሃፍቱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና አስረክበዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት “በአምስት ቀን አምስት ሺህ መጽሀፍ” በሚል ሃሳብ ባካሄደው የመጽሃፍ ማሰባሰብ መርሃ-ግብር ከእቅዱ በላይ መጽሃፍት ማሰባሰብ ችሏል፡፡

ውጤቱ ለሌሎች ተቋማት አርአያ እንደሚሆን ገልጸው፤ ከነገ ጀምሮ “እድሜ ልክ” የተሰኘ የመጽሐፍ ማሰባሰቢያ መርሀ-ግብር ይጀመራል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቭርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው የአብርሆት ቤተ መጽሃፍት እስከ አራት ሚሊዮን መጽሐፍ የመያዝ አቅም አለው ብለዋል።

ቤተ-መጽሃፉ ለበርካታ ዜጎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ካለው ፍላጎት አንጻር በተለያዩ አካባቢዎች ተጨማሪ ቤተ መጸሃፍቶች እንደሚያስፈልጉም ነው የገለጹት፡፡

ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2014 ለአንድ ወር የሚቆይ የመጽሐፍ ማሰባሰቢያ መርሀ-ግብር እንደሚዘጋጅም ተገልጿል። በመጽሃፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩም እስከ አንድ ሚሊዮን መጽሀፍት ለማሰባሰብ እቅድ ተይዟል።

Amharic English