Skip to content Skip to sidebar Skip to footer

የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ (ዩኒሳ) የኢትዮጵያ ለአብርሆት ቤተ-መጻህፍት የተለያዩ መጻህፍትን አበረከተ

የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ (ዩኒሳ) የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ለአብርሆት ቤተ-መጻህፍት የተለያዩ መጻህፍትን አበረከተ።

የዩኒቨርስቲው ተወካይ ፕሮፌሰር ቴኒሰን ሙጉቺኒ፤ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ መጽሃፍቶቹን አስረክበዋል።

መጽሃፍቶቹ ከ1 ሺህ 100 በላይ ሲሆኑ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ይዘት ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ተወካይ ፕሮፌሰር ቴኒሰን ሙጉቺኒ፤ የትምህርት አሰጣጥ በመማሪያ ክፍሎች ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ ሰዎች እንዲያነቡ ቤተ መጽሃፍቶችን ሙሉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዩኒሳ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ያደረገው ድጋፍም ለዚሁ ተግባር አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።

የአብርሆት ቤተ መጻህፍት ዳይሬክተር ኢንጂነር ውባየሁ ማሞ፤ ዩኒሳ ለአብርሆት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Amharic English