ዛሬ የመከላከያ ሚኒስቴር 3,500 በላይ መፀሀፍቶችን ለአብርሆት ቤተመጻህፍት አበረከተ።
የመከላከያ ሚኒስቴር ዶ/ር አብርሀም በላይ ለአብርሆት ቤተመጻህፍት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ በመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያቤት መፀሀፍቶቹን አስረክበዋል።
መጽሀፍቶቹ ከመከላከያ ጤና መመሪያ፣ከመከላከያ ዋር ኮሌጅ፣ከመከላከያ ዩኒቨርሲቲ እና ከሚኒስትሩ በግል ተነሳሽነት የተበረከቱ መሆናቸውን ተመላክቷል።
ሚንስትሩ መፀሀፍት ለሀገር እድገት ትልቅ ሚና እንደሚያበረክት እናም አብርሆት ቤተመጻህፍት ለማህበረሰቡ እውቀትን የሚቀስሙበት ፣ የሚያጎለብቱበት እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የአብርሆት ቤተ-መጻህፍት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ውብአየሁ ማሞ በበኩላቸው ለሀገር ለውጥ ቁልፍ መሳሪያ ለሆነው የትምህርት ግብ መሳካት አንባቢ ትውልድ መገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል።
የተሻለች ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያነብ ትውልድ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት መከላከያ ያደረገው ድጋፍ አስተዋጾኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ለአብርሆት ቤተ-መጻህፍት የሚደረጉ የመጽሐፍት ልገሳዎች ተጠናክረው እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የአብርሆት ቤተ-መጻህፍት የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሀም በላይ በግል ተነሳሽነት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የእውቅና ሰርተፊኬት አበርክቶላቸዋል።
2 Comments
abdulsemed nasir
ባጣም ዳስ ይላል
Gelana debela
This really amazing and unforgotable monument for the next generation and can build genetion to convince ideas through table round than combating at the battle feild which never end througj out over the world and also still it is not enough and need expantion like this one.
Thank and keep it up.