የማኅበረሰብ አንቂው አቶ ስዩም ተሾመ ከ3.66 ሚሊዮን ብር በላይ እና 4 ሺህ 953 የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መጽሐፍት ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ድጋፍ አድርጓል።
አቶ ስዩም ገንዘቡን እና መጽሐፍቱን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር አሰባስቦ ለአብርሆት ማስረከቡን ገልጿል።
ድጋፉን የተረከቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ እና የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ፣ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።