Skip to content Skip to sidebar Skip to footer

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መፃሕፍት ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት አበረከተ።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መፃሕፍት ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት አበረከተ።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቪግኒ ተርዮክኢን ጨምሮ ሌሎች የኤምባሲው ተወካዮች በተገኙበት መፃሕፍቶቹ ለአብርሆት ቤተ መፃሕፍት ተበርክተዋል።

የተበረከቱት መጽሃፍት በሩሲያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰባሰቡ መፅሃፍት መሆናቸው ተገልጿል።

አምባሳደሩ በሁለገቡ የአብርሆት ቤተ መፃሕፍት ባደረጉት ጉብኝት ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸውን መፅሃፍትን በማስረከባቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ለሁሉም ጉዳዮች ቁልፍ መሳሪያ ለሆነው ትምህርት ትኩረት በመስጠት አንባቢ ትውልድ መገንባት ወሳኝ መሆኑን እና
በተለይም አብርሆት ቤተመፃሕፍት የልጆች ማንበቢያ ክፍል መኖሩ ታዳጊዎች መጽሐፍትን እንዲያገላብጡ፣ የዕይታ አድማሳቸው እንዲሰፋና ዓለምን እንዲገነዘቡ ያስችላቸዋል ነው ያሉት።

በ እለቱ የቤተመፃሕፍቱ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ዉብአየሁ ማሞ ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው መፀሐፍቶቹን ተረክበዋል።

በተጨማሪም ዳይሬክተሩ ምክንያታዊና መረጃ ያለው ትውልድ ለመገንባት ሀገር በቀል መፃህፍቶችን ብቻ ሳይሆን እንደዚህ ያሉ አለም አቀፍ ይዘት ያላቸዉ መፃሕፍት ያሰፈልጋሉ ብለዋል።

Amharic English