Skip to content Skip to sidebar Skip to footer

“Modernizing Knowledge, Empowering Readers.”

የአብርሆት ቤተ- መጽሐፍ የአራት አመት የስኬት ጉዞን ምክንያት በማድረግ  የ“Abrehot Integrated Library Management System” እና “Abrehot Research Submission and review System” ይፋዊ የምርቃት ግብዣ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።

ክቡራን እና ክቡራት፤

የአብርሆት ቤተ መጽሐፍትን አገልግሎት ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ እና ተደራሽ የሚያደርገው “Abrehot Integrated Library Management System” እና “Abrehot Research Submission and review System” እንዲሁም ከ JSTOR Public Library ጋር በመተባበር ያለ አንዳች ክፍያ የቤተ መጽሐፍቱ አባል በመሆን በስልክዎ የሚጠቀሙበትን ዲጂታል ቤተ- መጽሐፍ በኦንላይን መጠቀም እንዲችሉ ለማስጀመርና  በይፋ የምናስመርቅበት ልዩ ስነ-ስርዓት ተዘጋጅቷል።

ይህ ሶፍትዌር የቤተ-መጽሐፍቱን አሰራር ወደ ዲጂታል ምዕራፍ የሚያሸጋግርና የእውቀት ተደራሽነትን የሚያሰፋ ታሪካዊ ስራ ነው። በዚህ የቴክኖሎጂ ሽግግር ወቅት ተገኝተው የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

📅 ቀን፡ 25/04/2018  🕒 ሰዓት፡ ክ 3፡00 ጀምሮ 📍 ቦታ፡ አብርሆት ቤተ መጽሐፍት ውስጥ

Amharic English