Skip to content Skip to sidebar Skip to footer

አብርሆት ቤተመጻሕፍት የአለም አቀፉን የሲልክ ሮድ የቤተመጻሕፍቶች ጥራት ጥምረትን ተቀላቀለ።

ቤተመጻሕፍቱ ይህንን ጥምረት የተቀላቀለው ከተገነባ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ጥራትና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት በመቻሉ መሆኑን መቀመጫውን ቻይና ያደረገው የሲልክ ሮድ አለም አቀፍ የቤተመጻሕፍት ጥምረት ይፋ አድርጓል።

አለም ላይ ከተገነቡት ቤተመጻሕፍት መካከል አብርሆት ቤተመጻሕፍት በአጭር ጊዜ የአለም አቀፉን ማህበረስብ የጥናት፣የምርምር፣የፈጠራ እንደዚሁም የጥንታዊ መፅሃፍት መገኛ በመሆን ትኩረት መሳብ እንደቻለ የገለፀው ይሄው የሲልክ ሮድ የቤተመጻሕፍት አለም አቀፍ ጥምረት ተቋሙ የኢትዮጵያ ቤተ መፅሃፍት ብቻ ሳይሆን የደመቀ የእውቀት መዳረሻ ቦታ ነው ሲል ገልፆታል።

ይህም 43ኛ ቤተመጻሕፍ ተቋማት ጥምረት ሆኖ መመዝገብ መቻሉን የሲልክ ሮድ አስታውቋል።

አብርሆት ቤተመጻሕፍት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሃሳብ አመንጭነትና ድጋፍ ለምረቃ በቅቶ አንፀባራቂ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ የገለፀው የአለም አቀፉ የቤተመጻሕፍት ጥምረት በአሁኑ ጊዜ ሶስት መቶ ሽህ በላይ የሃገር ውስጥ የጥናትና ምርምር ውጤቶች፣መቶ ሃያ ሽህ በላይ አለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን የያዘ ከመሆኑም ባሻገር በውስጡ ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊየን በላይ መፅሃፍቶችን መያዙንም ተቋሙ በዘገባው አስታውቋል።

የአብርሆት ቤተመጻሕፍት አስገራሚ ግንባታና አቀማመጥ እንደዚሁም ዙሪያ ግቢው የተላበሰው አረንጓዴያማ ገፅታ የተቋሙን ሞገስ ከፍ ከማድረጉም በላይ የዜጎች የንባብ ፍላጎት እንዲነሳሳ እንደሚጋብዝም የአለም አቀፉ የቤተመጻሕፍት ጥምረት ሲልክ ሮድ አያይዞ ገልፆአል።

አብርሆት ቤተመጻሕፍት በቀን ከ10 ሽህ በላይ አንባቢዎችን እያስተናገደ የ24 ሰዓት ግልጋሎት የሚሰጥ ግዙፍ ተቋም ነው።

Amharic English