አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት የህግ ታራሚዎች በዕውቀት እንዲበለጽጉ እንዲሁም በስነምግባር እንዲታነፁ ለማድረግ ከቃሊቲ ፌደራል ማረሚያ ቤት ጋር በቋሚነት መስራት ጀመረ።
የቤተ-መጽሐፍቱ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደርና ከታራሚዎች ጋር ባደረጉት ሰፊ ውይይት እንደገለፁት የህግ ታራሚዎች የፍርድ ግዜያቸውን በንባብ እንዲያሳልፉ ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። የህግ ታራሚዎች በእርማት በጊዜያቸው እንዲሁም ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ አምራች ዜጋ እና ከራሳቸው አልፈው ማህበረሰቡን የሚያገለግሉ ለማድረግ አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ተነሳሽነቱን ወስዶ ከተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ጋር ከፍተኛ ስራ እንደሚሰራ በተጨማሪ አሳስበዋል።
በውይይቱ ወቅትም አብርሆት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተፃፉ ወቅታዊ የስነ ልቦና ፣ የስነ ምግባር ፣ የስነ አዕምሮ፣ የስነ ሰብ ፣ ኪነ ጥበብ፣ የፍልስፍና፡ የሳይንስ ና ቴክኖሎጂ መጽሀሕቶችን ጨምሮ ሌሎች መጽሐፍቶችን ለታራሚዎች ተደራሽ እንዲሆን የበለጠ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በዚህም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርና ታራሚዎች ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸውና ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዳይሬክተር ያላቸውን የላቀ አድናቆት ገልፀዋል።
Abrehot Library started working with Kaliti Federal Penitentiary in order to enrich the knowledge and morals of the inmates of the law.
The director of the library Engineer Wubayehu Mamo mentioned that it is necessary to do a lot of work so that the inmates of the law can spend their time in reading. He further emphasized that Abrehot Library will take the initiative and work closely with various prisons to make the inmates of the law become productive citizens and serve the community beyond during their correctional period and when they join the society.
During the discussion, the director mentioned that Abrehot will do more to make books accessible to the inmates, including latest books on psychology, ethics, psychatry, humanities, art, philosophy, science and technology. With this, the prison administration and the inmates felt great joy and expressed their great appreciation for the director of the Abrehot Library