Skip to content Skip to sidebar Skip to footer

የአብርሆት ቤተ መጻህፍት የዲጂታላይዜሽን አገልግልት ሥራ ጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ዳይሬክተር ኢንጅነር ዉብአየሁ ማሞ በአብርሆት ቤተ መጻህፍት የዲጂታላይዚሽን አገልግሎት ሥራ አስጀምረዋል ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቤተ መጻህፍቱ አሁን በሚሰጠው አገልግሎት በአማካይ በቀን ከ15 ሺህ በላይ አንባቢዎችን የሚያስተናግድ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዛሬ በተጀመረው እና 80 ሺህ መጻህፍት ዲጂታል በተደረጉበት አገልግሎት ደግሞ ከእጥፍ በላይ አንባቢዎችን መድረስ ያስችላል ነው ያሉት።

“ትውልዱ የሚያነብበት ስፍራ በማጣቱ እንጂ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት በንባብ ራሱን ለማነጽ የሚተጋ መሆኑን በማየታችን፤ ተጨማሪ አዳዲስ ቤተመጻህፍት በየክፍለ ከተሞቻችን እየገነባን የተጠናቀቁትንም በቁሳቁስ እንዲሟሉ በማድረግ አንባቢ እና ምክንያታዊ ትውልድ ማፍራታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

Amharic English