ዛሬው እለት በአብርሆት_ቤተመጻሕፍት አዘጋጅነት የተጀመረው የመፅሃፍት አውደ ርዕይ በተሳካ ሁኔታ ተከፈተ።
በዝግጅቱ ላይ በርካታ የመፅሃፍ ደራሲያን ፣ ተርጉሚያን፣ አንባቢያንያ እና ሀያሲያን ተገኝተዋል፣ እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመፅሃፍ ወዳጆች ተገኘተዋል።
ይህ ዝግጅት ታህሳስ 18/ 2018 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 25 / 2018 ዓ.ም. ድረስ ይቆያል።
ሁሉም የመፅሃፍ ወዳጆች በዚህ ስምንት ቀናት ውስጥ መጥተው በተለያዩ የመፅሃፍ መደብሮች የቀረቡ መፅሃፎችን ማየት፣ መምረጥ መግዛተ እና ማንበብ ይችላሉ።
የዝግጅቱ ዝርዝር መረጃ
- ዓይነት: የመፅሃፍ አውደ ርዕይ (መጽሃፍ ገበያ)
- አዘጋጅ: አብርሆት ቤተ መፅሃፍት
- ቀን: ታህሳስ 18 -25.
- ቦታ: አብርሆት ቤተ መፅሃፍት
ሁሉንም የመጽሃፍ ወዳጆች እንድትጎበኙና እንድትሳተፉ እንጋብዛለን!
አብርሆት_ቤተመጻሕፍት








