የአብርሆት ቤተ-መጽሀፍት 4ተኛ ዓመት ክብረ በዓልን በማስመልከት ለ2ተኛ ጊዜ በህጻት ክፍል ውስጥ ደማቅ ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን በፕሮግራሙ መጀመሪያ የቤተመጽሀፍቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ታሪኩ የፕሮግራሙን መክፈቻ ንግግር ለወላጆችና ለህጻናት በመናገር ዝግጅቱ በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል፡፡ ከተዘጋጁት ፕሮግራሞች ዉስጥም የልጆች ማንበብ ፕሮግራም የተለያዩ ህጻናት የግጥም እና ስነ-ጽሁፍ ፤ ጨዋታዎች፤ ከ በርትና ኤልሞ ጋር የመዝሙር፣የዳንስ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የተረት መጽሀፍ እንብበው አሳልፈዋል ፡፡
በመጨረሻም ከሸገር ሰርከስ የመጡ ሰርከስ ትርዒት አቅራቢዎች ለህጻናቱና ወላጆች ደማቅ ሰርከስ ትርዒት አቅርበዋል፡፡








