Skip to content Skip to sidebar Skip to footer

ግንቦት 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለሁለተኛ ጊዜ ያሰባሰባቸውን ከ2 ሺህ በላይ መጽሐፍት ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት አበረከተ።

የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ሳሙኤል ወልደጊዮርጊስ መጽሐፍቱን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የአብሮሆት ቤተ መጽሀፍት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ለሆኑት ዶክተር ታምራት ሀይሉ አስረክበዋል።

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ከ13 ሺ 400 በላይ መጽሐፍት ማበርከቱን አስታውሰው፤ በጠቅላላው በሁለት ዙር የተበረከተው መጽሐፍት ቁጥር ከ15 ሺህ 700 በላይ መሆኑንም ተናግረዋል።

መጽሐፍቱ የታሪክ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የፍልስፍና፣ የሀይማኖት፣ የምርምርና የትምህርት አጋዥ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የክልሉን ብሄር ብሄረሰቦች ታሪክና ዕእሴት የሚያጎሉ መጽሐፍት በትኩረት መሰብሰባቸውንም ነው የተናገሩት።

ድርጅቱ መጽሐፍቱን ያሰባሰበው ከተቋሙ ሰራተኞች፣ ከተባባሪ አካላት፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከሀይማኖትና የትምህርት ተቋማት እንዲሁም ከግለሰቦች መሆኑ ታውቋል።

ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት “ሚሊዮን መጽሐፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ” በሚል መሪ ኃሳብ መጽሐፍትን ለማሰባሰብ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በርካታ ተቋማትና ግለሰቦች ምላሽ እየሰጡ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Amharic English